Fana: At a Speed of Life!

የ10ኛው የጣና ፎረም ቅድመ ጉባኤ ውይይቶች መካሄድ ጀመሩ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 4 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ የሚመክረው የጣና ፎረም ጉባኤ የቅድመ ውይይቶች መካሄድ ጀምሯል።

ቅድመ ውይይቱ በቀድሞው የዛምቢያ የነፃነት ታጋይ እና ፕሬዚዳንት በነበሩት ኬኔት ካውንዳ የትግል እና የመሪነት ታሪክ ላይ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

የውይይቱን መክፈቻ ኬንያዊው ፓን አፍሪካኒስት ምሁር እና የጣና ፎረም ቦርድ አባል ፓትሪክ ሎቾ ኦቲዬኖ ሉሙምባ የመሩት ሲሆን፥ የቀድሞ የዛምቢያ ፕሬዚዳንት የልጅ ልጅ ማዱላ ካውንዳ ተገኝተዋል።
የታሪክ እና የፖለቲካ ምሁሩ ሲሺዋ ሲሺዋ ካውንዳ በኬኔት ካውንዳ ላይ ያተኮረ ገለፃ አድርገዋል።

ከ300 በላይ የሃገር ውስጥ እና የውጭ እንግዶች የሚሳተፉበት የዘንድሮው 10ኛው የጣና ፎረም ጉባኤ በባህር ዳር ከተማ በነገው ዕለት በይፋ እንደሚከፈት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃላቀባይ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.