Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል ከ748 ሺህ ኩንታል በላይ ስንዴ በበጋ መስኖ ለማምረት ታቅዷል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በደቡብ ክልል በተያዘው ዓመት ከ748 ሺህ ኩንታል በላይ ስንዴ በበጋ መስኖ ለማምረት መታቀዱ ተገለፀ፡፡

በክልሉ “አዲስ እሳቤ ለግብርናችን ሽግግር “በሚል መሪ ቃል የግብርና ሴክተር የ2015 ሴክቶራል ጉባኤ በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ እየተካሄደ ነው ፡፡

በጉባኤው በደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር እንደገለጹት÷ በክልሉ በአበባና አትክልት ልማት፣ በእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት፣ በቡናና ቅመማ ቅመም ምርት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማጎልበት ተችሏል፡፡

በተያዘው ዓመትም ከ22 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በማልማት ከ748 ሺህ ኩንታል በላይ ስንዴ በበጋ መስኖ ለማምረት መታቀዱን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ጌትነት በጋሻው እንዳሉት ÷ በዞኑ ከ242 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በሰብል የተሸፈነ መሆኑን ጠቁመው ቡና፣ ኮረሪማ፣ ሰሊጥ፣ የቁም እንስሳት እና ሌሎች የግብርና ግብዓቶችን በስፋት ለማዕከላዊ ገበያ እየቀረበ ነው ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.