የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ  ኮሮና ቫይረስን አስመልክተው ከጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር  ተወያየዩ

By Meseret Demissu

March 22, 2020

አዲስ አበባ፣መጋቢት 13፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ኮሮና ቫይረስን አስመልክተው ከጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴን  ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ  በትናንት ምሽት ውይይታቸው ÷በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከጣሊያን ሕዝብ ጎን ነን ብለዋል፡፡

አያይዘውም የዓለም ማኅበረሰብ እንደ መሆናችን፣ ይህንን ሁኔታ በመተባበር እና በአንድነት ድል እንነሣዋለን ማለታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።