Fana: At a Speed of Life!

በመንግሥት ተቋማት የሚገኙ ቁርጥራጭ ብረቶችና ከአገልግሎት ውጪ የሆኑ ተሽከርካሪዎች የመሸጫ ዋጋ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በመንግሥት ተቋማት የሚገኙ ቁርጥራጭ ብረቶችና ከአገልግሎት ውጪ የሆኑ ተሽከርካሪዎች የመሸጫ ዋጋ ይፋ ሆነ።

የማዕድን ሚኒስቴር እና የመንግስት ግዥ እና ንብረት ባለስልጣን ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በመግለጫው በኢትዮጵያ ያለው የብረት ክምችት እየተጠና እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

ጥናቱ እስከሚያልቅም የውጭ ምንዛሬን ለማስቀረት በሃገር ውስጥ ያሉትን ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ ብረት እና የብረት ቁርጥራጮችን ለመጠቀም ተወስኖ ወደ ስራ ተገብቷል ብለዋል።

የመንግስት ግዥ እና ንብርት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሀጂ ኢብሳ በበኩላቸው፥ ማንኛውም የብረት ቁርጥራጭ እና ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ለሽያጭ እንዲያቀርቡ ለ169 የመንግስት ተቋማት እና ለ36 የመንግስት የልማት ድርጅቶች በየክልሉ ለሚገኙ የፋይናንስ ተቋማት መመሪያው መተላለፉንና ወደ ስራ መገባቱን ተናግረዋል፡፡

በእስካሁኑ የጥናት ሂደት የመሸጫ ዋጋው እንደየብረት አይነቶችና የገበያው ሁኔታ የመሸጫ ዋጋ ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት እንደየብረት አይነቶቹ በኪሎ ግራም የተወሰነ ሲሆን ስቲል 64 ብር፣ ካስት አይረን 51 ነጥብ 75 ብር ፣ ስክራፕ ያደረገ ተሽከርካሪ ወይም ማሽነሪ እና ያገለገለ ተሽከርካሪ ወይም ያገለገለ ማሽነሪ 51ነጥብ 25 ብር ሆኗል።

ከፌደራል እስከታችኛው ድረስ በመንግስት መስሪያ ቤቶች እና ተጠሪ ቋማት እንዲሁም በግለሰብ ደረጃ ያሉ ንብረቶችን ለገበያ የማይቀርቡ ከሆነ ተጠያቂነትን ያስከትላል ተብሏል።

ኢትዮጵያ በየዓመቱ ከውጭ ብረት ለማስገባት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የምታወጣ ሲሆን በ2013/14 ዓመተ ምህረት ብቻ 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ማውጣቷ በመግለጫው ተነስቷል።

በምንይችል አዘዘው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.