የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ አረንጓዴ ልማት ዲፕሎማሲ የወጣቶች ልዑክ ጂቡቲ ገባ

By Melaku Gedif

October 14, 2022

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 4 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ወንድማማችነት እና የአረንጓዴ ልማት ዲፕሎማሲ አላማ ለማስተዋወቅ የኢትዮጵያ የወጣቶች ልዑክ ጂቡቲ ገብቷል፡፡

የልዑካን ቡድኑ አበላት ጂቡቲ አመቦሊ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በጂቡቲ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ባለስልጣን አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ እና የጂቡቲ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ኢትዮጵያ በጎረቤት ሀገራት ለምታደርገው የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ መርሐ ግብርን ለመከወን ወደ ጅቡቲ ያቀናው ልዑካን ቡድን ዛሬ ረፋድ ላይ ጂቡቲ መድረሱን ከብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በጎረቤት ሀገራት እየተከናወነ የሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ በሁለቱ ሀገራት ያለውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ከማጠናከሩም በተጨማሪ ጠንካራ ወንድማማችነት እና አንድነትን ያጠናክራል ተብሎ ይጠበቃል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!