Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የተመሰረተበት “የአፍሪካ አዳራሽ” እድሳትን የማስጀመር ስነ ስርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 4 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የተመሰረተበት “የአፍሪካ አዳራሽ” እድሳትን የማስጀመር ስነ ስርዓት በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡
 
እድሳቱ ከ60 ዓመታት በላይ የቆየውን አዳራሽ ታሪካዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ ዘመኑን የዋጀ ገጽታ እንዲላበስ ያስችለዋል ተብሏል፡፡
 
በተለይም የአፍሪካን ታሪካዊ አመጣጥ፣ አህጉሪቱ አሁን ያለችበትን እና የወደፊት ሁኔታ የሚያሳይ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
 
የአፍሪካ ታሪክ፣ ባህል እንዲሁም ቅርሶች ለአህጉሪቱ ኢኮኖሚ እድገት የራሳቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ መስራት እንደሚገባም በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ ተገልጿል፡፡
 
የፕሮጀክቱ ዳይሬተር ካርሎስ ሃዳድ፥ አዲሱ የእድሳት ዲዛይን ዘላቂ፣ ማራኪ እና ጎብኚዎችን በሚስብ መልኩ የተቀረጸ መሆኑን አንስተዋል፡፡
 
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋየ ይልማ በበኩላቸው፥ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ለአፍሪካ አዳራሽ እድሳት አስፈላጊውን የግንባታ አቅርቦት በማዘጋጀቱ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
 
አዳራሹ ፓን አፍሪካኒዝም ተቋማዊ ቅርጽ የያዘበት መሆኑን የገለጹትሚኒስትር ዴኤታው፥ የምንፈልጋትን አፍሪካ ዕውን ለማድረግ ቁርጠኛ መሆን አለብን ብለዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.