የሀገር ውስጥ ዜና

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ባፉት 3 ወራት 411 ጊጋ ዋት ሰዓት አመነጨ

By Tamrat Bishaw

October 14, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት ከመነጨው አጠቃላይ የኤሌክትሪክ ኃይል የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 10 በመቶ አስተዋጽኦ ማበርከቱን የኃይል ማመንጫዎች ኦፕሬሽን ሥራ አስፈጻሚ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

በጽህፈት ቤቱ የዕቅድ ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ ጥሩወርቅ ሺፈራው እንደገለጹት÷ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከመነጨው 4 ሺህ 98 ጊጋ ዋት ሰዓት ኢነርጂ ውስጥ የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 411 ጊጋ ዋት ሰዓት አመንጭቷል፡፡

በቅርቡ ኃይል ማመንጫት የጀመሩት ሁለት ዩኒቶች እያንዳንዳቸው 375 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያላቸው ሲሆን÷ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 411 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል በማመንጨት ወደ ብሔራዊ ኃይል ቋት ማስገባት መቻሉን የኤሌክትሪክ ኃይል መረጃ አመላክቷል፡፡