የሀገር ውስጥ ዜና

38 አይነት ምርቶች ላልተወሰነ ጊዜ የውጭ ምንዛሬ እንዳይፈቀድላቸው ተወሰነ

By Shambel Mihret

October 14, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስቴር 38 አይነት ምርቶች የባንክ መተማመኛ ሰነድ እንዳያገኙ መወሰኑን አስታወቀ።

ምርቶቹ የብሄራዊ ማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ጉሙሩክ ኮሚሽን በጥናት ለይቶ ይፋ ያደረጋቸው ናቸው ተብሏል።

በምርቶቹ ላይ እገዳ የተጣለው ቅድሚያ የሚሰጣቸው ሆነው ስላልተገኙና የቅድሚያ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ገቢ እቃዎች በቂ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት ነው።

ምርቶቹ ለሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ምክንያት እንደሆኑም ብሔራዊ ባንክ ገልጿል፡፡

የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዢና ዋና ኢኮኖሚስት ፈቃዱ ድጋፌ እንደገለጹት ÷ እገዳው ላልተወሰነ ጊዜ የሚቆይ ነው ።

እገዳ የተጣለባቸው መጠጦች (ውስኪ ወይም ቢራ እና ሌሎች አልኮል መጠጦች)፣ ማስቲካ፣ ቸኮሌት፣ ውሃ፣ ሲጋራ፣ ሰው ሰራሽ ማጌጫዎችና መሰል ቁሳቁስ መሆናቸው ተጠቁሟል።

በግለሰቦች ኤል ሲ ተከፍቶባቸው የሚገቡ መኪናዎችንም እገዳው ይመለከታል ነው የተባለው።

ለባንኮች አዲስ ኤል ሲ እንዳይከፍቱ ደብዳቤ እየተሰራጨ እንደሆነ ምክትል ዋና ገዢው ተናግረዋል።

ባንኮች ከሰኞ ጀምሮ እንዲተገብሩም መመሪያ ተላልፏል፡፡

በአፈወርቅ እያዩና በጥበበሥላሴ ጀምበሩ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!