Fana: At a Speed of Life!

በየጊዜው የነበሩት የኢትዮጵያ መንግስታት ለአፍሪካ ህዝቦች ነጻነት ጽኑ አቋም አላቸው- አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አሁን ያለውም ሆነ በየጊዜው የነበሩት የኢትዮጵያ መንግስታት ለአፍሪካ ህዝቦች ነጻነት ጽኑ አቋም አላቸው ሲሉ የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ገልፀዋል።

“የደህንነት ስጋቶችን መቀነስ፣ ችግሮችን መቋቋም የምትችልና የምንመኛትን አፍሪካ መገንባት” በሚል መሪ ቃል የጣና ፎረም የቅድመ ፓናል ውይይት ዛሬ በባህር ዳር ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

አቶ ሃይለማርያም በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት “ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ ተምሳሌት ናት” ሲሉ ተናግረዋል።

በየመንግስታቱ የተስተዋለው መላ አፍሪካውያን ከቅኝ አገዛዝ ነጻ እንዲወጡ የማገዙ ሥራ እስካሁን ድረስ ተጠናክሮ የቀጠለ መሆኑንም ነው ያመለከቱት።

በዚህም ኢትዮጵያ ሌሎች የአፍሪካ የነፃነት አርበኞችን በማስተባበር ለፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ ተምሳሌት መሆኗን በተግባር ጭምር ያስመሰከረች ሀገር ናት ማለታቸውን የኢዜአ ዘገባ አመላክቷል።

የፎረሙ አወያይ ፕሮፌሰር ፓትሪክ ሉሙምባ በበኩላቸው “የዛንቢያው ኬኔት ካውንዳ፣ የጋናው ክዋሜ ንክሩማህ፣ የታንዛኒያው ጁሌስ ኔረሬና ሌሎች የአፍሪካ መሪዎች ለአህጉሪቱ ነጻነት የሰሩ ናቸው” ብለዋል።

የአፍሪካን ሰላምና ደህንነት ማረጋገጥ፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ትስስርን መፍጠርና ከውጭ ተጽዕኖ የተላቀቀ ፖለቲካል አስተሳሰብ መገንባት እንደሚገባም ፕሮፌሰር ፓትሪክ ገልጸዋል።

ለዚህም እንደ ጣና ፎረም ባሉ መድረኮች ችግር ፈቺ የሆኑ ሃሳቦችን በማመንጨትና የሚቀርቡ ሀሳቦችን በግብአትነት መጠቀም አስፈላጊ መሆኑን ነው ያስገነዘቡት።

በፎረሙ የቅድመ ፓናል ውይይት ላይ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.