Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያ ላይ የሚያራምደው አቋም መርህ አልባነቱን ያሳየ ነው – ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያ ላይ የሚያራምደው ኢ- ፍትሃዊ አካሄድ የህብረቱን መርህ አልባነት በግልጽ ያሳየ ነው ሲሉ የፖለቲካ ሳይንስና አለም ዓቀፍ ግንኙነት ተንታኞች ተናገሩ፡፡

የህብረቱ አባል ሃገር የሆነችው አየርላንድ የምታንጸባርቀው አቋም ተቀባይነት እንደሌለውም ነው የዘርፉ ተመራማሪዎች ያብራሩት፡፡

የፓለቲካ ሳይንስና አለም ዓቀፍ ግንኙነት አጥኝዎቹ አቶ ዘላለም ጌታቸው እና ሱራፌል ጌታሁን÷ የሽብር ቡድኑ ህወሓት የፓለቲካ ድለላ ስራ በህብረቱ በገሃድ ይታያል የሚል እምነትም አላቸው፡፡

የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የውስጥ ችግሮችን አስመልክቶ ሲከተላቸው የቆየው ፖለቲካዊ አሰላለፍም ግልጽ የሆነ ፖለቲካዊ ውግንና የታየባቸው እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

የሰሜኑን ጦርነት በተመለከተ የፌደራል መንግስት ለሰላም ያለውን ቁርጠኝነት ሲያረጋግጥ መቆየቱንም አንስተዋል የዘርፉ ባለሙያዎች፡፡

በዋናነት የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያን አስመልክቶ የሚያንጸባርቃቸው አቋሞች የህብረቱን መርህ አልባ አካሄድ የሚያመላክት እንደሆነ ተንታኞቹ ተናግረዋል፡፡

ይህ አካሄድ ደግሞ አየርላንድን የመሰሉት እንቆምለታለን ከሚሉት የሰብዓዊ መብቶችና ሌሎች በሃገራት የውስጥ ያለመግባት አለም ዓቀፍ መርሆዎችን የተጣረሰ እንደሆነም ተመራማሪዎቹ ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ መሰል የዲፕሎማሲና ፓለቲካዊ ጫናዎችን በጠንካራ ስራዎች ልትመክት እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

በውጭ ያሉ ዲፕሎማቶችና ሌሎች ልዑካንን በመጠቀም እውነታውን ማሰረዳት ይገባልም ነው ያሉት ምሁራኑ፡፡

ብሄራዊ ጥቅምን ያስቀደመ አካሄድን መከተል እንደሚገባም ሃሳባቸውን አካፍለዋል፡፡

በአወል አበራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.