Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት እያስከተለ ያለው ጥፋት በቃህ ሊባል ይገባል ሲሉ በወላይታ ሶዶ ከተማ የሚኖሩ የትግራይ ክልል ተወላጆች ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት እያስከተለ ያለው ጥፋት በቃህ ሊባል እንደሚገባው በወላይታ ሶዶ ከተማ የሚኖሩ የትግራይ ክልል ተወላጆች ተናገሩ።

በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያካሄዱት ተወላጆቹ፥ የሽብር ቡድኑ በንፁሃን ዜጎች ላይ እያደረሰ ያለውን ተደጋጋሚ በደል አውግዘዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች የሽብር ቡድኑ በንፁሃን ዜጎች ላይ በተለይ በወጣቱ ላይ እያደረሰ ያለውን በደል እና እልቂት እንደሚቃወሙ ተናግረዋል።

“ሁላችንም የምንመኘውን ሁለንተናዊ ሰላም ለማምጣት ከፋፋይ አጀንዳዎችን ወደጎን ልንተው ይገባናል” ያሉት ተሳታፊዎቹ፥ መንግሥት በሆደ ሰፊነት የዜጎችን እና የሀገርን ደህንነት በማስቀደም ለሰላም እያሳየ ያለውን ቁርጠኝነት እናደንቃለን ብለዋል።

የትግራይ ክልል ሕዝብ ሰላም እና ልማት ፈላጊ መሆኑን በመጥቀስም ለዚህም ይህን አስከፊ ቡድን ከሥልጣን ለማስወገድ እና አሁን ለመጣው ለውጥ እኩል ዋጋ የከፈለ እና የታገለ ሕዝብ መሆኑን አመላክተዋል።

አሸባሪ ቡድኑ እየፈጸፀመ የሚገኘውን ተግባር አውግዘው መንግሥት እየወሰደ ያለውን የመከላከል እርምጃ በቻሉት ሁሉ እንደሚደግፉ አረጋግጠዋል።

ህወሓት ከአፈጣጠሩ ጀምሮ የሰላምና አንድነት ዕሳቤ የማይዋጥለት ቡድን መሆኑን አመላክተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.