Fana: At a Speed of Life!

10ኛው የጣና ፎረም ጉባኤ በባህር ዳር ከተማ መካሄድ ጀምሯል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 10ኛው የጣና ፎረም ጉባኤ በባህር ዳር ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

ፎረሙ በአፍሪካ የሰላም፣ ጸጥታ እና ደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራል።

በፎረሙ ትናንት “የደህንነት ስጋቶችን መቀነስ፣ ችግሮችን መቋቋም የምትችልና የምንመኛትን አፍሪካ መገንባት” በሚል መሪ ቃል የጣና ፎረም የቅድመ ፓናል ውይይት ተካሂዷል።

በፎረሙ ላይ ለመካፈል የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት ባህር ዳር መግባታቸው ይታወሳል።

በተጨማሪም የአሁን እና የቀድሞ የሀገራት መሪዎች፣ ከተለያዩ የአፍሪካ ክፍል የመጡ ተመራማሪዎች እና ፖለቲከኞች ባህር ዳር ገብተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.