Fana: At a Speed of Life!

ኪዩር ኢትዮጵያ ለ3 ሺህ 200 ሕጻናትና ወጣቶች የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት ማቀዱን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኪዩር ኢትዮጵያ በዚህ ዓመት የአካል ጉዳትና ህመም ላለባቸው 3 ሺህ 200 ሕጻናትና ወጣቶች የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት ማቀዱን አስታወቀ።

ኪዩር ኢትዮጵያ ትናንት ለ46 አካል ጉዳተኛ ሕጻናትና ወጣቶች ዘመናዊ የሰው ሰራሽ አካል ድጋፍ አድርጓል።

የኪዩር ኢትዮጵያ የህጻናት ሆስፒታል ዋና ስራ አስኪያጅ ዐደይ አበበ÷ ሆስፒታሉ ለሕጻናትና ወጣቶች የአጥንትና ቆዳ ህክምና እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

በተለይም የእጅና እግር ጉዳት ላለባቸው ሕፃናትና ወጣቶች የሕክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

በተለያዩ ክልሎች ከሚገኙ ማገገሚያ ማዕከላትና ሪፈራል ሆስፒታሎች ተጎጂዎች ወደ ሆስፒታሉ እንደሚመጡ አስታውሰዋል፡፡

ኪዩር ኢትዮጵያ በየዓመቱ ለ3 ሺህ ሕጻናትና ወጣቶች ነፃ ሕክምና የሚሰጥ መሆኑን በማስታወስ በ2015 ዓ.ም ለ3 ሺህ 200 ታካሚዎች ነፃ ሕክምና ለመስጠት ማቀዱን ጠቁመዋል።

የሰው ሰራሽ አካል ድጋፍ የተደረገላቸው ህፃናት በበኩላቸው÷አካል ጉዳተኝነት ከመማር፣ ከመስራትና ያለምነውን ከማሳካት አይገድበንም ሲሉ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.