ስፓርት

በሴካፋ ከ17 ዓመት በታች የደረጃ ጨዋታ ታንዛኒያ ዩጋንዳን አሸነፈች

By Tamrat Bishaw

October 15, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተካሄደ በሴካፋ ከ17 ዓመት በታች የደረጃ ጨዋታ ታንዛኒያ ዩጋንዳን በማሸነፍ የዘንድሮውን መርሐ ግብር ሦስተኛ ሆና አጠናቀቀች፡፡

መደበኛው የጨዋታ ጊዜ አንድ አቻ መጠናቀቁን ተከትሎ ቡድኖቹ ወደ መለያ ምት አምርተዋል፡፡

በዚህም በተሰጠ የመለያ ምት ታንዛኒያ ዩጋንዳን 4ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የዘንድሮውን ከ17 ዓመት በታች የሴካፋ ውድድር ሦስተኛ ሆና አጠናቃለች፡፡

የፍጻሜ ጨዋታው በሶማሊያ እና በደቡብ ሱዳን መካከል የሚካሄድ ይሆናል፡፡

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ማኅበራት ምክር ቤት (ሴካፋ) ከመስከረም 23 ቀን 2015 ጀምሮ በአበበ በቂላ ስታዲየም እየተካሄደ ይገኛል።

በውድድሩ አንደኛ እና ሁለተኛ የሚወጡ ሀገራት በመጋቢት ወር 2015 ዓ.ም በአልጄሪያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ከ17 ዓመት በታች የእግር ኳስ ውድድር ዞኑን ወክለው የሚሳተፉ ይሆናል፡፡