የሀገር ውስጥ ዜና

ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡላቸውን የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሣይንስ ተፈታኞች እየተቀበሉ ነው

By Tamrat Bishaw

October 15, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በሁለተኛው ዙር የተመደቡላቸውን የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሣይንስ ተፈታኞች መቀበል ጀምረዋል፡፡

በዚህም÷ ጎንደር፣ ወሎ፣ ወልዲያ፣ ደብረ ታቦር፣ ደብረ ማርቆስ፣ ደብረ ብርሃን፣ እንጅባራ፣ ዲላ፣ አርባምንጭ፣ ዋቸሞ፣ ወራቤ፣ ሠመራ፣ ጅማ፣ ቡሌ ሆራ፣ አዲስ አበባ ሣይንስና ቴክኖሎጂ፣ ሰላሌ፣ ጋምቤላ፣ አሶሳ እና ደንቢ ዶሎ ዪኒቨርሲቲዎች ዛሬ የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሣይንስ ተማሪዎችን መቀበል ጀምረዋል፡፡

የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሣይንስ ፈተና ከጥቅምት 8 እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር ያወጣው መርሐ ግብር ያመላክታል፡፡