Fana: At a Speed of Life!

ጤና ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ ለመከላከያ ሠራዊት ከ112 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጤና ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ ለመከላከያ ሠራዊት ከ112 ሚሊየን ብር በላይ በጥሬ ገንዘብ እና በዓይነት ድጋፍ አደረጉ፡፡

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ድጋፉን ለመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ አስረክበዋል።

ድጋፉ 110 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ ሲሆን ከ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ያህሉ ደግሞ የዓይነት ነው፡፡

ዶክተር ሊያ እንደገለጹት÷ ለኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት ለሚዋደቀው ለጀግናው መከላከያ ሠራዊት ሁለንተናዊ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ነን፡፡

ባለፉት ሁለት ወራት ከ118 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የመድኃኒት ስርጭት መደረጉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.