የሀገር ውስጥ ዜና

በገበታ ለሐረር ጁገል የዓለም ቅርስ ከ3 ሚሊየን ብር በላይ ተሰበሰበ

By Tamrat Bishaw

October 15, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረር ጁገል ቅርስን በተቀናጀ መልኩ ለመጠበቅ ገበታ ለሐረር ጁገል የዓለም ቅርስ በሚል በተጀመረው የገቢ አሰባሰብ እስካሁን ከ3 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አብዱልባሲጥ አቡበከር እንደገለጹት÷ ቅርሱን ለመጠበቅ እየተሠራ ባለው ሥራ እስካሁን ከኩፖን ሽያጭ ብቻ ከ3 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል፡፡

የሐረር ተወላጆች እንዲሁም ኢትዮጵያውያን ቅርሱ ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ ማቅረባቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።