Fana: At a Speed of Life!

በግብርናው ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ለተጀመረው የብልጽግ ጉዞ መሳካት ጠቋሚ ናቸው – አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራልና የክልል ህግ አውጪ አካላት በጅማ ዞን ሸቤ ወረዳ በሩዝ ምርት የለማ ማሳን እየጎበኙ ነው፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የተሳተፉት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ÷ የስንዴ ልማት ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች በግብርናው ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ሀገሪቷ ለጀመረችው የብልጽግ ጉዞ መሳካት ጠቋሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በጅማ ዞን ሸቤ ወረዳ ያለው የሩዝ ልማት ሌሎች አካባቢዎችም ተሞክሮ እንደሚሆን የጠቆሙት አቶ ታገሰ÷ የውስጥ ችግራችን መነሻ የሆነውን ድህነት ለማስወገድ በግብርናው ዘርፍ እየተሰራ ያለው ስራ አበረታች መሆኑን ገልፀዋል።

የፌደሬሽን ሞክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ የያዘችውን ግብ ለማሳካት ክልሎች ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ ነው ብለዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በኦሮሚያ ክልል በስንዴ ልማት እየተሰራ ያለው ስራ አመርቂና ተስፋ ሰጪ መሆኑን ነው የተናገሩት።

የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ሰአዳ አብዱራህማን÷ በክልሉ የሚሰሩ የግብርና ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ ከግብዓት አቅርቦት ጀምሮ ሙያዊ ድጋፍና ክትትል እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.