Fana: At a Speed of Life!

በአምስተርዳም ማራቶንን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 6 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአምስተርዳም ማራቶንን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡

አትሌት አልማዝ አያና ርቀቱን 2 ሰዓት 17 ደቂቃ 20 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመጨረስ በአምስተርዳም ማራቶን የውድድሩን ሪከርድ በመስበር አንደኛ ወጥታለች።

አልማዝ አያና ከወሊድ፣ ከጉዳት እና ከከባድ የጉልበት ቀዶ ጥገና በኋላ ነው የአምስተርዳም ማራቶን ውድድርን ሪከርድ በመስበር በቀዳሚነት ያጠናቀቀችው፡፡

በተመሳሳይ ገንዘቤ ዲባባ ውድድሩን በሁለተኝነት ስታጠናቅቅ÷ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊ አትሌት ጸሀይ ገመቹ ደግሞ ሶስተኛ ወጥታለች።

በተመሳሳይ÷በወንዶች ምድብ በተካሄደው ውድድር ደግሞ አትሌት ፀጋዬ ጌታቸው ርቀቱን 2:4:49 ጊዜ በመግባት በአንደኝነት ሲያሸንፍ አትሌት ባዘዘው አስማረ በ2:4:57 ሰዓት የሶስተኝነት ደረጃን አግኝቷል::

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.