Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማህበር የአፍሪካ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 7 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማህበር የአፍሪካ ዳይሬክተር ፓትሪክ የሱፍ ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸው የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦትን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ አስታውቀዋል።

በተጨማሪም ማህበሩ በኢትዮጵያ በሚሰጣቸው ሁሉን አቀፍ አገልግሎቶች ዙሪያ መወያየታቸውንም ነው የገለጹት።

በኢትዮጵያ ሰብአዊ ድጋፍን ተደራሽ ለማድረግ እና በሰላም ሂደቱ የሚገኙ ለውጦችን ታሳቢ ያደረጉ አገልግሎቶችን ማሻሻል በሚቻልባቸው ጉዳይ በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ እንደሆኑም ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.