Fana: At a Speed of Life!

ሀገራዊ የምክክር ሂደቱን ስኬታማ ለማድረግ የሶስትዮሽ ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገራዊ የምክክር ሂደቱን ስኬታማ ለማድረግ የሶስትዮሽ የጋራ መግባቢያ ስምምነት ተፈርሟል፡፡

የሰላም ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት እና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሀገራዊ ምክክር ሂደቱን ስኬታማ ለማድረግ የሶስትዮሽ የጋራ መግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ታዬ ደንደአ፣ የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ዋና ዳይሬክተር ሄኖክ ፍስሀ እና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ ዶክተር አቡዱልቃድር አደም ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ ሀገራዊ የምክክር ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን በትብብር ለመስራት የሚያስችል ነው መባሉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.