የሀገር ውስጥ ዜና

ሰንደቅ ዓላማ አንድ ሀገር ነፃነቱን እና ሉዓላዊነቱን የሚያሳይበት ነው – ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ

By Feven Bishaw

October 17, 2022

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 7 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰንደቅ ዓላማ አንድ ሀገር ነፃነቱን እና ሉዓላዊነቱን የሚያሳይበትም ነው ሲሉ ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ።

የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን የብዙሃንነታችን መገለጫ፣ የሉዓላዊነታችን ምሰሶ” በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ15ኛ ጊዜ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እየተከበረ ነው።

ሰንደቅ ዓላማ አንዱ ሀገር ከሌላው ሀገር የሚለይበት ፣ የሌላው ተገዢ አለመሆኑን የሚያረጋግጥበት የነፃነት እና የሉዓላዊነት መገለጫ ነው።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እየተከበረ በሚገኘው የሰንደቅ ዓላማ ቀን ፕሬዝዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ አባት አርበኞች ፣ የመከላከያ ሰራዊት እና ሌሎች የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።