Fana: At a Speed of Life!

ሰንደቅ ዓላማችን የግዛት አንድነት እና የብሔራዊ መግባባት መገለጫ ዓርማችን ነው – አቶ ጃንጥራር አባይ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 7 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰንደቅ አላማ ቀን ሰንደቅ አላማችን የብዝሐነታችን መገለጫ፤ የሉዓላዊነታችን ምሰሶ ነው በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ከተማ በድምቅት ተከብሯል፡፡

በስነ-ስርዓቱ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ቡዜና አልቃድር ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የስራ ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ እንዲሁም ሌሎች የምክር ቤቱና የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ተገኝተዋል።

አቶ ጃንጥራር ዜጎች ለሀገራቸው ያላቸው ፍቅርና ብሔራዊ ስሜት ለሰንደቅ ዓላማ በሚሰጡት ክብር እንደሚገለጽ አውስተዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን ለሰንደቅ ዓላማ የምንሰጠው ፍቅርና ክብር ከእናት ከአባቶቻችን በክብር የወረስነው፤ ለቀጣዩ ትውልድ በክብር የምናወርሰው፤ በልባችን ውስጥ ታትሞ የሚቆይ የብዝሃነታችንና የአንድነታችን የሉዓላዊነታችን መገለጫ ታላቅ ሀገራዊ ዕሴት ነው ብለዋል፡፡

ሰንደቅ ዓላማችን የግዛት አንድነት ፣ የአብሮነት የብሔራዊ መግባባት መገለጫ ዓርማችን ነው ያሉት አቶ ጃንጥራር÷ ማንኛውም ዜጋ ለሰንደቅ ዓላማ ክብር የመስጠት፣ ማክበርና የማስከበር ኃላፊነት እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡

በዓሉ የውስጥ ቅጥረኞችና ተላላኪዎቻቸው ብሔራዊ አንድነታችን እና ሉዓላዊነታችንን አደጋ ላይ ለመጣል እየሰሩ ባለበት ወቅት መከበሩ ለሕብረ ብሄራዊ አንድነታችን መጠናከርና መነቃቃት ትልቅ ትርጉም እንዳለው ማንሳታቸውን የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.