የሀገር ውስጥ ዜና

የሱዳን መንግስት የኢትዮጵያን ህዝብ እና መንግስት በሚጎዱ ማናቸውም ተግባር ላይ ተባባሪ አይሆንም – የሱዳን መረጃ ኤጀንሲ ኃላፊ

By Amele Demsew

October 17, 2022

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 7 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳን መንግስት የኢትዮጵያን ህዝብ እና መንግስት በሚጎዱ ማናቸውም ተግባር ላይ ተባባሪ አይሆንም ሲሉ የሱዳን መረጃ ኤጀንሲ ኃላፊ ሜጀር ጀኔራል መሀመድ አሊ አህመድ ገለጹ፡፡

ሜጀር ጀኔራል መሀመድ አሊ ከኢትዮጵያ የመረጃ እና ደህንነት ሀላፊዎች ጋር በፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይታቸውም፥ ሜ/ጄ መሀመድ አሊ በሁለቱ ሀገራት ድንበር መካከል በተደጋጋሚ የሚነሱ ግጭቶችን ለመፍታት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸው፥ የሱዳን መንግስት የኢትዮጵያን ህዝብ እና መንግስት በሚጎዱ ማናቸውም ተግባር ላይ ተባባሪ እንደማይሆን አረጋግጠዋል።

የሁለቱ ወገኖች በቀጣይ በሁለቱ ሀገራት የመረጃ ተቋማት መካከል ሊሰሩ ስለሚገባቸው ጉዳዮች ተወያይተው ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ከመከላከያ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡