Fana: At a Speed of Life!

የምዕራብ ጎጃም ዞን ለመከላከያ ሰራዊት ከ18 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ለመከላከያ ሰራዊት ከ18 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ምግብ ነክ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

የዞኑ የንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አሰፋ ጥላሁን ÷ በዞኑ ከሚገኙ 21 ወረዳዎች 18 ሚሊየን 75ሺህ 600 ብር የሚገመት በሶ፣ ቆሎ ፣ ውኃ፣ ተምርና ብስኩት ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል።

እንዲሁም የምዕራብ ጎጃም ዞን ማኅበረሰብ የእርድ እንስሳትና ደረቅ ሬሽን በማቅረብ ለመከላከያ ሰራዊቱ ያለውን ደጀንነት እያሳየ ይገኛል ብለዋል።

አሸባሪው ሕወሓት እስከሚደመሰስና ጦርነቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስም ዞኑ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸውን ከሰሜን ጎንደር ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ድጋፉን የተረከቡት የመከላከያ ሠራዊት ሎጅስቲክስ አስተባባሪ ኮሎኔል ሽመልስ ብርሃኑ÷ ድጋፉ ለመከላከያ ሰራዊቱ የጀርባ አጥንት መሆኑ ገልፀው ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.