Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም ክላውድ ቤዝድ ኮንታክት ሴንተር አገልግሎት አስጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 8 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም የደምበኞች አገልግሎትን በተለያዩ አማራጮች ማግኘት የሚያስችለውን የኮንታክት ሴንተር መፍትሄ በዛሬው እለት በሳይንስ ሙዚየም አስጀምሯል።

አገልግሎቱ ከዚህ ቀደም ደንበኞችን በድምፅና በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች የሚቀርቡ ጥያቄዎችን በተናጠል ያስተናግዱ የነበሩ የጥሪ ማዕከሎችን አሰራር ያዘመነና በልዩ ልዩ አማራጮች የሚቀርቡ የደምበኞችን ጥያቄ በአንድ ላይ አቀናጅቶ ለኮንታክት ሴንተር ወኪሉ በማቅረብ የቢዝነስ ተቋማት ለደምበኞቻቸው ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስችል ነው ተብሏል።

አገልግሎቱ በአምስት ቋንቋዎች ለተገልጋዩ ተደራሽ የሚሆን ሲሆን በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገጾች የተጠየቁትን ጥያቄዎች ሰብስቦ በአንድ ቋት ለተቋሙ በማድረስ የተገልጋዩን ጥያቄ መመለስ የሚያስችል የደምበኞች አገልግሎት ነው።

ከዚህ ቀደም የነበረው የኮንታክት ሴንተር አገልግሎት ድምፅ ላይ ብቻ ትኩረት ያደረገ ቢሆንም በአዲሱ ክላውድ ቤዝድ ኮንታክት ሴንተር ግን በሁሉም የማህበራዊ ትስስር ገጾች አገልግሎቱን ተቋማት ለደምበኞች ማድረስ ይችላሉ ተብሏል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ መሠል የአገልግሎቶች ሀገሪቱ እየገነባች ለምትገኘው የዲጂታል ኢኮኖሚ የራሱን አስተዋፅኦ ያበረክታል ብለዋል።

አገልግሎቱ ከዚህ ቀደም ደምበኞች ወደ ጥሪ ማዕከል ደውለው ወረፋ በመጠበቅ የሚያጠፉትን ጊዜም በመከላከልና ደምበኞች በፈለጉት ጊዜ መጠቀም ይችላሉ ተብሏል።

ኢትዮ ቴሌኮም በዓለም ላይ የቴሌኮም አገልግሎት ከሚሰጡ 780 ኦፕሬተሮች መካከል 23ኛ እንዲሁም ከአፍሪካ ደግሞ ከናይጄሪያ ቀጥሎ በ2ኛ ደረጃ ይገኛል ብለዋል።

በአለምሰገድ አሳዬ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.