Fana: At a Speed of Life!

በሲዳማ ክልል በቡና ልማት ለሚሰሩ አካላት የዕውቅና እና የምስጋና ሥነ-ስርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል ለ45 ቡና አምራቾች ፣ ላኪዎች ፣ ተቋማት እና ባለሙያዎች የዕውቅና እና የምስጋና ሥነ- ስርዓት ተካሄደ።

በ2014 በጀት ዓመት 27 ሺህ ቶን የታጠበ እና ያልታጠበ ቡና ከክልሉ ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረብ የቻለ ሲሆን ከዚህም 109 ሚሊየን ዶላር ማግኘት ተችሏል ነው የተባለው።

በዘንድው በጀት ዓመት ይህን አሃዝ በማሳደግ 50 ሺህ ቶን ለማቅረብ እየተሰራ እንደሚገኝ የክልሉ እርሻ እና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ መስፍን ቃሬ ተናግረዋል።

በእውቅና እና በምስጋና ሥነ -ስርዓቱ ላይ የሲዳማ ርዕሰ መስተደድር ደስታ ሌዳሞ ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በታመነ አረጋ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.