Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባ “በትምህርት ቤቶች የምገባ ፕሮግራም” ከ133 ከተሞች ጋር ተወዳድራ አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ “በትምህርት ቤቶች የምገባ ፕሮግራም” ምርጥ ተሞክሮ በ8ኛው የሚላን የከተማ ምግብ ፖሊስ ስምምነት ግሎባል ፎረም ዘላቂ አመጋገብ እና ሥነ ምግብ ዘርፍ አሸንፋለች፡፡

አዲስ አበባ ይህንን ሽልማት ያሸነፈችው በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ133 ከተሞች ጋር ተወዳድራ መሆኑ ታውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሽልማቱን በተቀበሉበት ወቅት÷ በኢትዮጵያ ቅድሚያ ለሰው የሚሰጥ ፖሊሲ በማውጣት እየተከናወነ ስላለው ሰው ተኮር ተግባራት ከሚላን የከተማ ምግብ ፖሊስ ስምምነት ፈራሚ ከተሞች ለመጡ ከንቲባዎች እና ተሳታፊዎች ልምድ አካፍለዋል።

በከንቲባ አዳነች አቤቤ የተመራ ልዑክ÷ “Food to Feed the Climate Justice: urban food solutions for a fairer world” በሚል መሪ ሐሳብ በብራዚል ሪዮ ዲጄኔሮ እየተካሄደ በሚገኘው 8ኛው የሚላን የከተማ ምግብ ፖሊስ ስምምነት ግሎባል ፎረም ላይ እየተሳተፈ ነው፡፡

 

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ከ133 ከተሞች አዲስ አበባ ማሸነፏን ጠቅሰው ድሉ የኢትዮጵያ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ ይህን ሽልማት ያሸነፈች ብቸኛ የአፍሪካ ሀገር መሆኗን ጠቁመው÷ ሽልማቱም የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የመላ የአፍሪካ ነው ብለዋል፡፡
ጉዳዩ ሀብታም ወይም ድሃ የመሆን ጉዳይ ሳይሆን÷ የመንግሥትን የፖሊሲ፣ የተግባር ቆራጥነት እና ካለው ውስን ሃብት ላይ ለዜጎች ቅድሚያ በመስጠት በተሠራው ሥራ የተገኘ ሽልማት መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ ለድሉ መገኘት አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።
Seen by Minale Berhanu at 3:58 PM
Enter
Write to Minale Berhanu

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.