በፕሪሚየር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ 4ኛ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ 4ኛ ተካታታይ ድሉን አስመዝግቧል፡፡
ቀን 7 ሰዓት በባህር ዳር ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ፈረሰኞቹ አዳማ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፈዋል፡፡
ኢስማኤል ኦሮ አጉሮ የቅዱስ ጊዮርጊስን ሁለት ጎሎች በጨዋታ እና በፍፁም ቅጣት ምት ሲያስቆጥር ዳዋ ሁቴሳ የአዳማ ከተማን ብቸኛ ጎል አስቆጥሯል፡፡
ቶጎአዊው የቅዱስ ጊዮርጊስ አጥቂ እስማኤል ኦሮ አጉሮ በአራት ጨዋታዎች 8 ጎል በማሰቆጠር የፕሪሚየርሊጉን ኮከብ ጎል አስቆጣሪነት ደረጃ ይመራል፡፡