Fana: At a Speed of Life!

የቆዳ ተረፈ ምርትን ወደ ኮላ ጥሬ እቃነት የሚቀይር ፋብሪካ ወደ ስራ ገባ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቆዳ ተረፈ ምርትን ወደ ኮላ ጥሬ እቃነት የሚቀይር ፋብሪካ ወደ ስራ ገብቷል፡፡

“ጂያዚን ዛንግ ክረስት ኤንድ ፊኒሽድ ሌዘር ፕሮዳክትስ” የተባለ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት ፋብሪካውን ወደ ስራ ማስገባቱ ተገልጿል፡፡

በዚህም የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አመራሮች እና ጋዜጠኞች ፋብሪካውን የጎበኙ ሲሆን÷ ምርቱ የውጭ ምንዛሬን ከማስገኘት ባለፈ በቆዳ ኢንዱስትሪዎች አካባቢ፥ የአካባቢ ብክለትን የሚያስከትሉ የደረቅ ቆሻሻ ክምችትን ይቀንሳል ተብሏል፡፡

እንዲሁም የተሻለ አመራረት ዘዴን ተግባራዊ ከማድረግ እና ሀብትን ከመጠቀም አንፃር የጎላ ሚና እንዳለው ተገልጿል።

ድርጅቱ በቆዳው ኢንዱስትሪ ዘርፍ ተሰማርተው ያለቀለት የቆዳ ምርትን በማምረት ወደ ውጪ ገበያ የሚልክ እና በውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት በቻይናውያን ባለሀብቶች የተመሰረተ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.