Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ ሁለት ቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላኖችን ለማስገባት በዝግጅት ላይ መሆኑን ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደፊት ሁለት ተጨማሪ ቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላኖችን ለማስገባት በዝግጅት ላይ መሆኑን ገለፀ፡፡

ቦይንግ 787 ድሪም ላይነር አውሮፕላን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመጀመሪያ ጊዜ በረራ የጀመረበት 10ኛ አመት ተከብሯል።

በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 787 ድሪም ላይነር አውሮፕላንን ወደ ስራ በማስገት በአፍሪካ በቀዳሚነት በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ከጃፓን ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ እንደነበር ተጠቁሟል።

በአከባበሩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ÷ ቦይንግ 787 እጅግ ዘመናዊና ለመንገደኞች ምቹ መሆኑን ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ካሉት 140 አውሮፕላኖች ውስጥም 27 አውሮፕላኖች ቦይንግ 787 ድሪም ላይነር አውሮፕላኖች መሆናቸውን ገልፀዋል።

የድርጅቱ አመራሮች ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ያላቸውን ግንኙነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

ቦይንግ 787 በፈረንጆች 2012 ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ ተመላክቷል፡፡

በሳሙኤል ወርቃየሁ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.