Fana: At a Speed of Life!

የገንዘብ ግሽበትን እና የጥቁር ገበያን ለመቆጣጠር የተዘረጉ አዳዲስ አሰራሮች አበረታች ናቸው – የምጣኔ ሀብት ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት የገንዘብ ግሽበትን እና የጥቁር ገበያን ለመቆጣጠር በቅርቡ ይፋ ያደረጋቸው አዳዲስ አሰራሮች እና የቁጥጥር መንገዶች አበረታች ናቸው ሲሉ የምጣኔ ሃብት ምሁራን ገለጹ።

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የምጣኔ ሀብት ምሁራን የገንዘብ ግሽበትን እና የጥቁር ገበያን ለመቆጣጠር የተዘረጉ አዳዲስ አሰራሮች እና የቁጥጥር መንገዶች አበረታች መሆናቸውን ገልጸው ሆኖም የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት ተጨማሪ ስራዎች መከናወን ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ የምጣኔ ሀብት መምህሩ ዶክተር መኮንን ካሳሁን እንዳሉት፥ የተዘረጉት አዳዲስ አሰራሮች በተለይ በባንኮች እና በጥቁር ገበያ መካከል ያለውን የምንዛሬ ልዩነት ማጥበብ የሚችሉ እና የውጭ ምንዛሬ ክምችትንም የሚያሻሽሉ ናቸው።

በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስት የኢኮኖሚክስ መምህሩ ረዳት ፕሮፌሰር ጥምቀቴ አለሜ በበኩላቸው እንዳሉት፥ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ከተከለከሉት የእቃ አይነቶች የሚገኘው ውጤት እንደ ሀገር ከሚፈለገው ውጤት አንጻር አነስተኛ በመሆኑ በቀጣይ ተጨማሪ የቅንጦት ምርቶች ላይ እገዳው መቀጠል አለበት።

የቁጥጥር ስራው መጠንከር በራሱ አዳዲስ የህገወጥ መንገዶች እንዲፈጠሩ ሊያደርግ ስለሚችል አስቀድሞ መፍትሄዎችን ማበጀት እና የሀገር ውስጥ ምርት ማሳደግ ይገባልም ብለዋል ምሁራኑ።

በትዕግስት አብርሃም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.