Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ስለሺ ከ50 በላይ የአሜሪካ ባለሃብቶች ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ እና የኢፌዴሪ የገንዘበ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ ከ50 በላይ የአሜሪካ ባለሃብቶች ጋር ተወያዩ፡፡

ባለሃብቶቹ በዚህ ወቅት እንዳሉት፥ ኢትዮጵያ ከአጎዋ መውጣቷ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ አብራርተዋል፡፡

በዚህም በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች ሥራ አጥ እንዲሆኑ የሚያደርግ ብቻ ሳይሆን የአሜሪካ ባለሃብቶች ከሥራ እንዲወጡ የሚያስገድድ እንደሆነም ነው የገለጹት፡፡

ይህም የኢትዮጵያንና አሜሪካን የረዥም ጊዜ ወዳጅነት እንደሚጎዳም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እና የኢትዮጵያን ህዝብ ኑሮ ለማሻሻል የማያወላውል አቋም እንዳለውም ነው ያነሱት፡፡

በዚህም አምባሳደሩ እና ሚኒስትሩ ፥ በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን ያፈሰሱ የአሜሪካ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የአጎዋ ተጠቃሚነት ላይ የተጣለው እገዳ እንዲነሳ ግፊት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.