Fana: At a Speed of Life!

የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ ከዩናይትድ ኪንግደም የልማት ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 9 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከዓለም ባንክ እና ከአይኤምኤፍ ጉባኤ ጎን ለጎን የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ ከዩናይትድ ኪንግደም የልማት ሚኒስትር ቪኪ ፎርድ ጋር በአሜሪካ ተወያዩ።

በወቅታዊ የኢትዮጵያ ፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ውይይት መካሄዱን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

አቶ አህመድ ሺዴ በዚህ ወቅት መንግስት ባካሄዳቸው የኢኮኖሚ የሪፎርም ስራዎች፣ ስለ ሰላም ሂደቱ፣ ባጋጠሙ ተግዳሮቶች ዙሪያ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ከዚህ ባለፈም ሪፎርሙን ለመተግበር እና ኢትዮጵያ የሚያጋጥሟትን ችግሮች ለመፍታት ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት፣ ሀገራት እና የልማት አጋሮች ድጋፍ አስፈላጊ መሆኑን ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል።

የዩናይትድ ኪንግደም የልማት ሚኒስትር ቪኪ ፎርድ በበኩላቸው መንግስት እያደረገ ያለውን ሪፎርም እንደሚያደንቁ ገልጸዋል።

አያይዘውም የሰላም ሂደቱን እንደሚደግፉ በመጥቀስ ብሪታንያ ለኢትዮጵያ ልማት የምታደርገውን ድጋፍ ትቀጥላለች ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.