የሀገር ውስጥ ዜና

ዶ/ር ሊያ ታደሠ የአዳሬ ጤና አጠባበቅ ጣቢያን ጎበኙ

By Meseret Awoke

October 19, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሠ በሐዋሳ ከተማ የሚገኘውን የአዳሬ ጤና አጠባበቅ ጣቢያን ጎበኙ፡፡

በጉብኝቱ ወቅት ፥ ተቋሙ እየሰጠ ያለው አገልግሎት በባለሙያዎች የተብራራ ሲሆን ፥ ጤና ጣቢያው የቤተሰብ ምጣኔ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነ ተጠቁሟል ።

በዚህም ከ5 ሺህ በላይ ሰዎች የረጅም ጊዜ የወሊድ አገልግሎት ማግኘታቸው መገለጹን ደሬቴድ ዘግቧል፡፡

ተቋሙ ያለው ግብዓትና የሰው ሃይል አቅም ከህብረተሰቡ ፍላጎት ጋር የሚመጣጠን አለመሆኑን ነው የበሽታ መከላከልና የቤተሰብ ዕቅድ ዘርፍ ባለሙያ ሊበን ገለልቻ የተናገሩት ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!