Fana: At a Speed of Life!

በግሉ ዘርፍ ላይ ያተኮረ አውደ ጥናት በአዲስ አበባ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ከዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ጋር በመተባበር በግሉ ዘርፍ ላይ ያተኮረ አውደ ጥናት በአዲስ አበባ ተካሄደ፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀጂ ኢብሳ በአውደ ጥናቱ ባደረጉት ገለፃ የግዥ ሂደት ላይ ግልፅነትን፣ ተጠያቂነትን እና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የመንግስት ግዥ ተግዳሮቶች ላይ የግሉ ዘርፍ ንቁ ተሳትፎ ያስፈልጋል ብለዋል ።

መሰል ተግዳሮቶችን ለመፍታት የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ህግና መመሪያን ማሻሻል መጀመሩን እና የመንግስት የኤሌክትሮኒክስ ግዥዎችን ማዘጋጀቱንም ተናግረዋል።

በአውደ ጥናቱ የዓለም ባንክ የግዥ ማዕቀፍን በተመለከተ ፣ የቢዝነስ እድሎች እና የንግድ ሥራዎች፣ ምርቶች እና አገልግሎቶች ፣ ስለ ሴክተር ደረጃ ምዘና እንዲሁም ከግሉ ዘርፍ የኢትዮጵያ የመንግስት ግዥ ህግ ማግኘት በሚችልባቸው አጀንዳዎች ዙሪያ ምክክር ተደርጓል፡፡

በተጨማሪ በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ፖርትፎሊዮ ላይ የቅሬታ አያያዝ ዘዴ ላይ በተለያዩ ጥናት አቅራቢዎች ገለፃ ተሰጥቶ ውይይት ተደርጎባቸዋል ።

 

በምንተስኖት ሙሉጌታ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.