በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፍተኛ አመራሮች የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የከፍተኛ አመራሮች የውይይት መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
የውይይት መድረኩ “በደም የተከበረ በላብ የታሠረ ዘላቂ ሰላምና ቀጣይነት ያለው ዕድገት የማረጋገጥ ውጥኖች” በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ በውይይቱ መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት÷ ባለፉት ዓመታት የሀገርን ክብርና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ የደም ዋጋ ተከፍሎበታል ብለዋል ።
ሉዓላዊነታችንን ለማስከበር ከሚከፈለው መስዋዕትነት ባሻገር በላብ የታሠረ ዘላቂ ሠላም እና ዕድገት ለማምጣት ሌት ተቀን መስራት ይገባልም ነው ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ።
በጫና ሳይበገሩ ሉዓላዊነቷን በማስከበር ኢኮኖሚውን የሚያሳድጉ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚያስፈልግ ጠቁመው÷ የሚስተዋለውን ሌብነት መታገልና ማረም እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የራስን አቅም በመገንባት ኢኮኖሚውን የሚያሻግር ተግባር መፈጸም ይገባል ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ÷ ከውጭ የሚገባ ስንዴን ለማስቀረት ዘርፈ ብዙ ስራዎች መሰራታቸውን አውስተዋል።
የችግሮችን ምንጭ በመለየት እና በመረባረብ በላብ የታሠረ ተግባር በመፈጸም ጠንካራ ኢኮኖሚ መገንባት ይገባል መባሉን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!