Fana: At a Speed of Life!

የዜጎችን ህይወት ለማሻሻልና ለሌሎች ዘርፎች መጎልበት ግብርና የማይተካ ሚና አለው – ር/መ ይልቃል ከፋለ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 9 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዜጎችን ህይወት ለማሻሻልና ለሌሎች ዘርፎች መጎልበት ግብርና የማይተካ ሚና እንዳለው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ የዜጎችን ህይወት ለማሻሻልና ለሌሎች ዘርፎች መጎልበት ግብርና የማይተካ ሚና አለው ብለዋል።

ከዘርፉ የሚገኘውን ምርት ለማሳደግ በኩታ ገጠም ስንዴ ሰብል ልማት ላይ ያደረግነው ርብርብ አበረታች ውጤት እየታየበት ነው ሲሉም ገልጸዋል።

በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን በጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ አርሶ አደሮች በኩታ ገጠም እየለማ ያለው የስንዴ ሰብል ተስፋ ሰጪ መሆኑን አስታውቀዋል።

ከግብርናው የሚገኘውን ውጤት በተፈለገው ደረጃ ለማሻሻል ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማድረግ ይኖርባቸዋልም ነው ያሉት።

ዘርፉን ለማዘመንና ውጤታማነቱን ለማሳደግ አዳዲስ የቴክኖሎጂ አማራጮችን ለክልሉ አርሶ አደሮች ለማቅረብ የምናደርገውን ጥረት አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.