የሀገር ውስጥ ዜና

በኦሮሚያ ክልል ለተጎዱ ወገኖችና ተቋማት የሚውል የ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ድጋፍ ተደረገ

By Meseret Awoke

October 19, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ለኦሮሚያ ክልል 1ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።

የተደረገው ድጋፍ በክልሉ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖችና ለወደሙ ተቋማት የሚውል መሆኑ ተገልጿል፡፡

ድጋፉን ያስረከቡት የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ኢ/ር ጫልቱ ሳኒ ሲሆኑ ፥ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ መረከባቸውን ከክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!