የሀገር ውስጥ ዜና

በለይቶ ማቆያ ማዕከላት ለሚቆዩና ወጪያቸውን መሸፈን ለማይችሉ ዜጎች መንግስት ሙሉ ወጪያቸውን ይሸፍናል – ኢንጂነር ታከለ

By Tibebu Kebede

March 23, 2020

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 14 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከኢትዮጵያ ውጭ የነበሩ ወገኖች በሚመለሱበት ጊዜ ወደ ህብረተሰቡ ከመቀላቀላቸው በፊት በለይቶ ማቆያ ማዕከላት በሚቆዩባቸው ጊዜዎች ወጪያቸውን መሸፈን ለማይችሉ ዜጎች ሙሉ ወጪያቸውን መንግስት እንደሚሸፍን አስታወቁ።

ኢንጂነር ታከለ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ መንግስት ከተለያዩ ሃገራት ወደ ኢትዮጵያ ለሚገቡ መንገደኞች እና ወገኖች የለይቶ ማቆያ ማዕከል ማዘጋጀቱን አስታውቀዋል።

በዚህ ወቅትም ለቆይታ ጊዜው ወጪያቸውን መሸፈን ለማይችሉ ዜጎች የከተማ አስተዳደሩ ሙሉ ወጪያቸውን እንደሚሸፍን ገልጸዋል።

ኢንጂነር ታከለ አያይዘውም በመተሳሰብ ራስን መጠበቅ እንደሚገባ ጠቅሰዋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision