Fana: At a Speed of Life!

እስራዔል የዩክሬንን የጦር መሣሪያ ጥያቄ ውድቅ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራዔል የጦር መሣሪያ ወደ ዩክሬን እንደማትልክ አስታወቀች፡፡

የእስራዔል ፍትኅ ሚኒስትር ጊዴኦን ሳኣር ÷ “ለዩክሬን የምናደርገው ድጋፍ የመሣሪያ አቅርቦትን አያካትትም ፤ በዚህ ላይ የአቋም ለውጥም አላደረግንም” ብለዋል፡፡

ቀደም ሲል የእስራዔል የዳያስፖራ ጉዳዮች ሚኒስትር የሆኑት ናችማን ሻይ ሀገራቸው ለዩክሬን የመሣሪያ ድጋፍ የምታደርግበት ጊዜ አሁን ነው ሲሉ መደመጣቸው ይታወሳል።

የእስራዔሉ የዳያስፖራ ጉዳዮች ሚኒስትር ናችማን ሻይ መግለጫ ÷ በሩሲያ ዘንድ ቁጣ መቀስቀሱም ነው የተሰማው፡፡

የቀድሞው የሩሲያ ፕሬዚዳንት ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ ÷ እስራኤል ለዩክሬን ወታደራዊ ድጋፍ የምታደርግ ከሆነ የሁለቱን ሀገራት ሁሉን ዓቀፍ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያበላሸዋል ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡

የመንግስት አካላት እስራኤል ዩክሬንን ለማስታጠቅ ዕቅድ እንደሌላት ለታይምስ ኦፍ እስራኤል መናገራቸውን አር ቲ ዘግቧል።

የእስራዔሉ የዳያስፖራ ጉዳዮች ሚኒስትር ናችማን ሻይ አስተያየት ፈፅሞ የመንግስት ፖሊሲዎችን አያንጸባርቅም ሲሉም መንግስታዊ ምንጮቹ አስተባብለዋል ነው የተባለው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.