Fana: At a Speed of Life!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት እና ጉህዴን የሠላም ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 9 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት እና በክልሉ ታጥቆ ሲንቀሳቀስ የነበረው የጉሙዝ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉህዴን) ችግሮችን በውይይት ለመፍታት የሚያስችል የሠላም ስምምነት ዛሬ ተፈራረሙ።
የሠላም ስምምነት ሠነዱን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን እና የጉሙዝ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉህዴን) ሊቀ መንበር አቶ ግራኝ ጉደታ በአሶሳ ከተማ ተፈራርመዋል።

በሠላም ስምምነቱ ላይ በመከላከያ ሠራዊት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮማንድ ፖስት አስተባባሪ ሜጀር ጀኔራል አምዴ ተገኝተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.