የሀገር ውስጥ ዜና

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት እና ጉህዴን የሠላም ስምምነት ተፈራረሙ

By ዮሐንስ ደርበው

October 19, 2022

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 9 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት እና በክልሉ ታጥቆ ሲንቀሳቀስ የነበረው የጉሙዝ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉህዴን) ችግሮችን በውይይት ለመፍታት የሚያስችል የሠላም ስምምነት ዛሬ ተፈራረሙ። የሠላም ስምምነት ሠነዱን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን እና የጉሙዝ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉህዴን) ሊቀ መንበር አቶ ግራኝ ጉደታ በአሶሳ ከተማ ተፈራርመዋል።

በሠላም ስምምነቱ ላይ በመከላከያ ሠራዊት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮማንድ ፖስት አስተባባሪ ሜጀር ጀኔራል አምዴ ተገኝተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!