Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ የተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀቁ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ የተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል፡፡

ቀን 7 ሰዓት የተደረገው የአርባ ምንጭ ከተማ እና የሀዲያ ሆሳዕና ጨዋታ ያለግብ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቅ ባህርዳር ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ ያደረጉት የከሰዓት መርሐ ግብር አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡

ድሬዳዋ ከተማ በያሬድ ታደሰ የፍፁም ቅጣት ምት ጎል እስከ መጨረሻዎቹ ደቂቃ ሲመራ ቢቆይም ዱሬሳ ሹቢሳ በ77ኛው ደቂቃ ላይ ጎል አስቆጥሮ ጨዋታው በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡

ፕሪሚየርሊጉን ቅዱስ ጊዮርጊስ በ12 ነጥብ ሲመራ ሀዲያ ሆሳዕና በ7 ነጥብ ይከተላል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.