የሀገር ውስጥ ዜና

በከንቲባ አዳነች አቤቤ የተመራ ልዑክ የC40 የዓለም ከንቲባዎች ፎረም ለመሳተፍ ቦነስ አይረስ ገባ

By Mikias Ayele

October 19, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተመራ የልዑካን ቡድን የC40 የዓለም ከንቲባዎች ፎረም ለመሳተፍ አርጀንቲና ቦነስ አይረስ ገብቷል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቦነስ አይረስ ከተማ ከከንቲባ ሆራቺዮ ሮድሪገዝ ላሬት እና ከአፍሪካ ልማት ባንክ የመሰረተ ልማትና የከተሞች ዕድገት ክፍል ኃላፊ ኦሌ ስቱድረፕ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

በውይይታቸውም÷ በተለይም በከተማ ዘመናዊ የቆሻሻ አወጋገድ እና የአየር ንብረት ጥበቃ ስርዓት እንዲሁም በትምህርት ሴክተር እና በትራንስፖርት ልማት ላይ በትብብር ለመሥራትና ልምድ ለመለዋወጥ መክረዋል፡፡

በተጨማሪም የከተሞቹን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተል፡፡

አዲስ አበባ ከC40 አባል ከተሞች አንዷ መሆኗ እና የአየር ንብረት ብክለትን የሚከላከሉ በርካታ ሥራዎችን እያከናወነች መሆኗ ተገልጿል፡፡