Fana: At a Speed of Life!

ቤቶች ኮርፖሬሽን እና ኢትዮ ቴሌኮም በትብብር በሚሠሩባቸው ጉዳዮች ላይ ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን እና ኢትዮ ቴሌኮም በተለያዩ የትብብር ማዕቀፎች ላይ አብረው ለመሥራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ተስማሙ፡፡

በስምምነቱ መሰረት÷ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ባካሄደው የተቋም ግንባታና ሪፎርም አሠራሩን ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይዝ ለማድረግ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ኢትዮ ቴሌኮም የሚደግፍ ይሆናል፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም የማኔጅመንት አባላት አጠቃላይ የኮርፖሬሽኑን የለውጥ ሥራዎችና የዲጂታል ዳታ ሴንተርን ጎብኝተዋል፡፡

ከኮርፖሬሽኑ ጋር በትብብር ለመሥራት ስምምነት ላይ በመደረሱ የተሰማቸውን ደስታ መግለጻቸውን የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ኮርፖሬሽኑ እያካሄደ ላለው የለውጥ ሥራ እና ዲጂታላይዜሽን ኢትዮ ቴሌኮም የዲጂታል አገልግሎቶችን ለኮርፖሽሬኑ ያቀርባል፡፡

የትብብር ስምምነቱን በአጭር ጊዜ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.