Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ ተመድ በዩክሬኑ ጦርነት ጥቅም ላይ የዋሉ ድሮኖችን የሚመረምር ቡድን እልካለሁ ማለቱን ተቃወመች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሩሲያ በዩክሬኑ ጦርነት ጥቅም ላይ አውላቸዋለች ያላቸውን ድሮኖችን የሚያጣራ ቡድን እልካለሁ ማለቱ ተቀባይነት የለውም ስትል ተቃወመች፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት የሞስኮ የድሮን አጠቃቀምን በተመለከተ ዝግ ስብሰባ አድርጓል፡፡

ይህንን ተከትሎም በተመድ የሩሲያ ምክትል አምባሳደር ዲሜትሪ ፖሊያንስኪ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ እና ደጋፊዎቻቸው ባልተገባ ምርመራ እጃቸውን እንዳያስገቡ ጠይቀዋል፡፡

የሩሲያ ጦር በዩክሬኑ ጦርነት የተጠቀማቸው ሰው አልባ አውሮፕላኖች የሩሲያ ስሪት የሆኑ እንጅ ከየትም የመጡ አይደሉም ሲሉ አምባሳደሩ ከስብሰባው በኋላ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡

ተመድና ምዕራባውያን ሩሲያ ከዩክሬን ጋር በገባችው ጦርነት የኢራን ስሪት የሆኑ ድሮን ተጠቅማለች በሚል ይወነጅላሉ።

ይህን ለማጣራትም ወደ ሩሲያ መርማሪ ቡድን የመላክ ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል።

ሩሲያም ይህን የሚያደርጉ ከሆነ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋር ያለንን ግንኙነት እንደገና ለማየት እገደዳለሁ ማለቷን ቲ አር ቲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.