Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ ረቂቅ አዋጅን ጨምሮ 3 ረቂቅ አዋጆችን ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መራ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ ረቂቅ አዋጅን ጨምሮ ሦስት ረቂቅ አዋጆችን ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቷል፡፡

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ተካሂዷል፡፡

ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው የቋሚ ኮሚቴዎችን አደረጃጀት ለማሻሻል የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብም መርምሮ ማጽደቁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በዚህም መሰረት የቋሚ ኮሚቴዎች ቁጥር ከ11 ወደ 13 ከፍ እንዲል ተደርጓል።

የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ለሕግ ፍትሕና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዋናነት ለሰው ሀብትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በተባባሪነት ለዝርዝር ዕይታ መርቷል።

በተመሳሳይ ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው ስለ እጽዋት ዘር ለመደንገግ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን፣ የግብርና ምርት አምራችና አስመራች ግንኙነት ለመወሰን የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ለግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር እይታ መርቷል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.