Fana: At a Speed of Life!

ሰዎችን ሲያግቱ የነበሩ 2 ግለሰቦች እያንዳንዳቸው በ12 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ማጠቢያ ንዑስ ወረዳ በተደጋጋሚ ሰዎችን

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ማጠቢያ ንዑስ ወረዳ በተደጋጋሚ ሰዎችን ሲያግቱ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች በ12 ዓመት ፅኑ እሰራት ተቀጡ፡፡

ወርቁ ድረሰ እና ታረቀኝ ሲሳይ የተባሉት ተከሳሾች ጥቅምት 21 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ አራት ሠዓት አካባቢ መተማ ወረዳ ማጠቢያ ንዑስ ወረዳ ጉባይ ጀጀቢት በተባለው ስፍራ ከሌሎች ያልተያዙ የፅንፈኛው የቅማንት ኮሚቴ ነን ከሚሉ ግብረ-አበሮቻቸው ጋር በመሆን የመኪናውን አሽከርካሪ እና የመኪናውን ባለቤት ማገታቸውን የመተማ ወረዳ የማጠቢያ ንዑስ ወረዳ የታክቲክ ምርመራ ክፍል ኃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር ጌታቸው አስረሴ መግለጻቸውን የወረዳው ፖሊስ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

ተከሳሾቹ ያገቷቸውን ሰዎችም ወደ ቋራ ወረዳ ኮዘራ ቀበሌ ቄሎ ሰፈር ከተባለው ቦታ በመውሰድ ለ11 ቀን አቆይተዋቸዋል፡፡

ከዛም ወደ ቤተሰቦቻቸው በማስደወል አንድ ሚሊየን አምስት መቶ ሺህ ብር መጠየቃቸው ነው የተገለጸው፡፡

የታጋች ቤተሰቦችም ከብዙ ድርድር በኋላ ሥድስት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር በመክፈል እንዳስለቀቋቸው ተጠቁሟል፡፡

ፖሊስም የወንጀሉ ድርጊት በጥቆማ ከደረሰው በኋላ ባደረገው እልህ አስጨራሸ ክትትል ወንጀለኞችን በጭልጋ ወረዳ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራውን በማጣራት ለማጠቢያ ንዑሰ ወረዳ ፍርድ ቤት መላኩ ተገልጿል።

ተከሳሾቹ ክስ ተመስርቶባቸው ሲከራከሩ ከቆዩ በኋላ ፍርድ ቤቱ ተከሳሾች ጥፋተኛ መሆናቸውን በቀረቡ ማስረጃዎች በማረጋገጡ ጥፋተኛ ብሏቸዋል፡፡

ፍድር ቤቱ ጥቅምት 10 ቀን 2015 ዓ.ም በዋለው ችሎትም ተከሳሾችን እና ሌሎችን ያስተምራል በማለት እያንዳንዳቸውን በ12 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ወስኖባቸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.