የሀገር ውስጥ ዜና

79 ኢትዮጵያውያን ከጅቡቲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By Feven Bishaw

October 20, 2022

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጅቡቲ ከሚገኘው የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ቢሮ ጋር በመተባባር 79 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ አድርጓል፡፡

ከተመላሾቹ መካከል 36ቱ ከየመን ወደ ጅቡቲ የገቡ ሲሆን÷ ቀሪዎቹ ደግሞ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ለመሻገር ያሰቡና ጅቡቲ ከገቡ በኋላ ሐሳባቸውን የቀየሩ መሆናቸው ተገልቷጿል፡፡

ባለፉት ሦስት ዓመታት ብቻ ከጅቡቲ በመነሳት ቀይ ባህርን በማቋረጥ ላይ እያሉ 6 የሕገ ወጥ አዘዋዋሪዎች የጀልባ መገልበጥ አደጋዎች ደርሰው ከ118 በላይ ኢትዮጵያውያን ለህልፈት መዳረጋቸውን የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡

የጉዞውን አስከፊነት በመገንዘብ ወጣቶች በሕገ ወጥ ደላሎች በመታለል ሕይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው በዚህ አደገኛ የጉዞ መስመር ከመንቀሳቀስ እንዲቆጠቡ ኤምባሲው መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡